Posts

ዓይኖች በእነዚህ ሰዎች ላይ ናቸው

Image
ከቢቢሲ የተገኘ ያሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታን ይዞ አልፏል። በመጀመሪያዎች የሳምንቱ ቀናት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ጠንካራ የሚባል የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ ተከናወነ። በቀጣዮቹ ቀናት በሽብር ወንጀል የተከሰሱና ተፈርዶባቸው የነበሩ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችም ተፈቱ። በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ የስልጣን ልልቀቅ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ተከትሎም አርብ ማምሻውን ደግሞ አነጋጋሪ የሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ። ከዚህ ሁሉ በኋላ ተሰናባቹን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ማን ይተካቸዋል የሚለው መነጋገሪያ ሆኗል። በርካቶችም በማህበራዊ ድረ-ገፆች እና መገናኛ ብዙሃን ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩን ሊተኳቸው ይችላሉ የሚሏቸውን ሰዎች ሲጠቅሱ ቆይተዋል። የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 73 ንዑስ አንቀጽ 1 ስለ ጠቅላይ ሚንስትሩ አሰያየም በግልጽ እንደሚያትተው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል ይመረጣል። ሊመረጥ የታሰበው ግለሰብ ግን የምክር ቤቱ አባል ካልሆነ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ቦርድ ሟሟያ ምርጫ እንዲያካሂድ ከጠየቀ በኋላ፤ ዕጩውን ግለሰብ በሟሟያ ምርጫው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኖ መመረጥ አለበት። ተሻሽሎ በወጣው የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም መሰረት የሟሟያ ምርጫ የሚካሄደው፤ በየደረጃው ያሉ የምክር ቤቶች በተለያየ ምክንያት የተጓደሉባቸውን አባላት እንዲሟሉላቸው ለምርጫ ቦርዱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም በሕጉ መሰረት የቀረበ የይውረድልን ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው። ቦርዱም ጥያቄው በደረሰው በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ የሟሟያ ምርጫ ያካሂዳል። ማሟያ ምርጫ ማለት በይውረድልን ወይም በማንኛውም ምክንያት በየደረጃው

በሲዳማ አሸባሪዎችን በመኪና አሳፍራችኋል በሚል ሁለት ሰዎች ታሰሩ

በሲዳማ አሸባሪዎችን በመኪና አሳፍራችኋል በሚል ሁለት ሰዎች ታሰሩ በደቡብን ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በሲዳማ ዞን የበንሳ ወረዳ ፖሊስ አሸባሪዎችን አሳፍራችሁ ወደ ከተማዋ አስገብታችኋል በሚል ሁለት ሰዎችን ማሰሩን የሲዳማ ሃርነት ንቅናቄ አስታወቀ፡፡ ሙሉ ሪፖርቱን እዚህ ተጭነው ይከታተሉ

#EBC ሰበር ዜና ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኢህአዴግ ሊቀመንበርነትና ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመነሳት ጥያቄ አ...

Image

በሐዋሳ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገነባው የሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ውዝግብ አስነሳ

ከ ሪፖርተር ጋዜጣ በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የሚገነባው የሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ፕሮጀክት የመሬት ይገባኛል ውዝግብ ተነሳበት፡፡ ሆቴሉ ሊገነባበት በታሰበበት ቦታ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ያነሳው የመከላከያ ሚኒስቴር መሆኑም ታውቋል፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር የሆነን ሆቴል በሐዋሳ ለመገንባት  የይሁንታ ደብዳቤ በከተማ አስተዳደሩ ተሰጥቶኛል የሚሉት ባለሀብቱ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው፣ ሆቴሉን ለማስገንባት ዲዛይን ለማሠራት ያደረጉት እንቅስቃሴ መደናቀፉን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ባለሀብቱ ሆቴሉን ለመገንባት ያሰቡትን መሬት ያገኙት ለኢትዮጵያ ሚሊኒየም በከተማ መስተዳድሩ ጥሪ በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ወቅት ነበር፡፡ በወቅቱ የከተማ መስተዳደሩ ባለሀብቱ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል እንዲገነቡበት ስምንት ሺሕ ካሬ ቦታ ሰጥቷቸዋል፡፡ ባለሀብቱም ይህንን ቦታ በ6,720,000 ብር አጠቃላይ ዋጋ የአምስት በመቶ ቅድሚያ ክፍያ በመክፈል በ2000 ዓ.ም. ተረክበው ነበር፡፡ ምንም እንኳን ባለሀብቱ በወቅቱ ከከተማው የተረከቡትን መሬት ለወጣቶች የመዝናኛ ማዕከል ለመገንባት አቅደው የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ ትልቅ ኢንቨስትመንት ውስጥ ለመግባት ወስነው የሆቴሉን ፕሮጀክት ይጀምራሉ፡፡ በዚህም መሠረት ይህን ዓለም አቀፍ ሆቴል ለመገንባት ለሁለት ዓመት ያህል የፈጀ ድርድር ከሆቴሉ ጋር አድርገዋል፡፡ ሆቴሉንም ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ለተደረገው ድርድር ከአሥር ሚሊዮን ብር በላይ ለአደራዳሪዎቹ ተከፍሏቸዋል፡፡ የከተማ መስተዳድሩንም የመዝናኛ ማዕከል ግንባታውን በሆቴል ፕሮጀክቱ መቀየር እንደሚችሉ ባለሀብቱ በደብዳቤ ጠይቀው፣ መስተዳድሩ ጳጉሜን 3 ቀን 2009 ዓ.ም. በጻፈላቸው ደብዳቤ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል

የቱሪስት አገልግሎት ጥራት መጓደል ለዘርፉ ዕድገት እንቅፋት መሆኑ ተገለጸ

Image
ፎቶ ከ ክልሉ ቱርዝም ቢሮ ከ ኢዜኣ የቱሪስት አገልግሎት ጥራት መጓደል በዘርፉ ዕድገት ላይ እንቅፋት እየሆነ መምጣቱን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም ገልፀዋል፡፡ ሀገሪቱ ያላትን የቱሪዝም ሃብት በማልማት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንዳልተቻለ የገለጹት ሚኒስትሯ፤ የቱሪስት አገልግሎቶች ጥራት መጓደል ዋነኛ እንቅፋት መሆኑን ተናግረዋል። "በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍና ቱሪስቶች ለሚከፍሉት ዋጋ ተመጣጣኝ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ ነው" ብለዋል። የቱሪዝም ልማት በርካታ ተግዳሮቶች ያሉበት ቢሆንም የቱሪዝም መስህቦችን አልምቶና አስተዋውቆ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገሪቱን ተወዳዳሪነትና የዘርፉን ገበያ ለማሳደግ ጥረቱ መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል። ለዚህም የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል የሆቴሎች የደረጃ ምደባ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ነው የገለጹት። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከዓለም ቱሪዝም ድርጅት ጋር በመተባበር ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው የሆቴሎች መስፈርት ማውጣቱን አስታውሰዋል። በዚህም በአምስት ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ 365 ሆቴሎች የኮከብ ደረጃ መስጠቱን ነው ያነሱት። በቀጣይም ለቱሪስቶች አገልግሎት የሚሰጡ አዳዲስ ሆቴሎች፣ ሎጆች፣ ሬስቶራንቶችና አስጎብኚ ድርጅቶች የደረጃ ምደባ እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል። ሀገሪቱ በቱሪዝም ዘርፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ያሉ ቸግሮችን መፍታት እንደሚገባም ዶክተር ሒሩት አመልክተዋል። የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አክመል አህመድ በበኩላቸው፤ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኝና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት በኩል ትከረት የተሰጠው ቀ