Posts

Ethiopia: First National Residency Matching Program for Medical Doctors

Image
Ethiopia, successfully executed National Residency Matching Program (NRMP) with a view to stepping up the health service accessibility, affordability and availability throughout the country. The program which is unprecedented in the medical history of the country conducted its first NRMP exam in selected exam hubs: Addis Ababa, Jimma, Mekelle, Bahirdar, Hawassa, and Haromaya. According to Dr. Wondowossen Eshetu, program advisor for medical education in Ministry of Health (MOH) previously general practitioners never had a chance to choose three areas of specialization in one shoot. But now they can go for such a chance taking three types of examinations. In the past, there were only 5 higher learning institutions which used to give residency programs across the country. Happily, now, the number has shot up to 12. According to the World Health Organization (WHO) the physician to inhabitants ratio for sub-Saharan country has to be one to ten thousand. Despite this standard Ethiopia

በደቡብ ሙስና የፈፀሙ 413 ተጠርጣሪዎች እስከ 17 ዓመት ተቀጡ

በደቡብ ክልል የሙስና ወንጀል የፈፀሙ 413 ግለሰቦች እስከ 17 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጥተዋል፡፡ በደቡብ ክልል በ2009 ዓመተ ምህረት ከሙስና እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ ክስ በተመሰረተባቸው 413 ተከሳሾች ላይ እስከ 17 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት መተላለፉን የክልሉ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ገለጸ። በክልሉ በጥልቅ ተሃድሶው ወቅት በተካሄደው የፀረ ሙስና እና ብልሹ አሰራር እንቅስቃሴ በተጋለጡት ግለሰቦች እስካሁን በ3 ሺህ 134 ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ሰለሞን ሃይሉ ዛሬ አስታውቀዋል። ከእነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ፖለቲካዊ እርማጃ የተወሰደባቸው ሲሆን፤ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደም ገልጸዋል። ሙስና ብልሹ አሰራር በመፈፀም የመንግስትን እና የሕዝብን ጥቅም ያሳጡ ግለሰቦች ላይ 211 መዝገብ ተከፍቶ 413 ተከሳሾች ላይ ህጋዊ ውሳኔ እንደተሰጠባቸውም አቶ ሰለሞን አስታውቀዋል፡፡ እነዚህም ከ17 ዓመት ፅኑ እስራት እስከ እስከ 3 ወር ቀላል እስራት እና እስከ ከ105 ሺህ 300 ብር የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸው ገልፀዋል፡፡ በክልሉ 291 ሚሊዮን 299 ሺህ 512 ብር ከምዝበራ ማዳን ተችሏል ነው ያሉት ሃላፊው፡፡ ገንዘቡ ተመዝብሮ በክትትል እንዲመለስ የተደረገ እና በጥቆማ ቀድመ መከላከል የተቻለ መሆኑንም አብራርተዋል። ከሙስና ጋር በተያያዘ መኖሪያ ቤቶች፣ ባለ ሁለት እና ባለ አራት ወለል ህንፃዎች፣ ፔኒሲዮን፣ ጥሬ ገንዘብ እና ተሸከርካሪዎች መታገዳቸውንም አቶ ሰለሞን አስታውቀዋል። ከገንዘብ ባሻገር በገጠር 10 ሺህ ሄክታር እና በከተማ 1 ሚሊየን ካሬ ሜትር መሬት ተመላሽ መደረጉንም ገልፀዋል፡፡ ህዝቡ ችግሮችን በማጋለጥ ረገድ ዋንኛ ተ

Ethiopia: 2017 Revised Humanitarian Requirements Snapshot (as of 8 August 2017)

Image
On 8 August 2017, the government of Ethiopia and humanitarian partners released the mid-year review of the Humanitarian Requirements Document (HRD) for 2017. Southern and eastern Ethiopia continue to battle the impact of the Indian Ocean Dipole-induced drought, exacerbated by disease outbreaks, large scale loss of livelihood assets and displacement. The dire situation was further compounded by below average spring rains, the third consecutive poor/failed rains in the southern drought belt. This left at least 8.5m people in need of relief food assistance through the year, up from 5.6m in January. Some US$ 487.7m is urgently required for the multisector response for the remainder of the year. Separately, some 4m Public Works clients of the Productive Safety Net Programme (PSNP) will also require sustained assistance to the end of 2017, at a cost of $300m. Read more  @

ዋሊያዎቹ በመጪው ዕሁድ ለቻን ዋንጫ ማጣሪያ ከሱዳን ጋር በሀዋሳ ይጫወታሉ

Image
የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ዋሊያዎቹ ለአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና ቻን ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታውን ከሱዳን አቻው ጋር በመጪው እሁድ ያደርጋል። 2018 በኬንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ይኸው ሻምፒዮና የሚካፈሉ አገራት ለመለየት የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታዎች ብቻ ይቀራሉ።   ዋሊያዎቹም ከሱዳን አቻው ጋር በሐዋሳ ዓለም አቀፍ  ስታዲየም እሁድ 10 ሰዓት ላይ  ወደ ቻን ለማለፍ ይጫወታል። በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሐዋሳ   ልምምዱን በማድረግ ላይ ነው። አሰልጣኙ ከዛምቢያ ጋር ባደረጉት  የአቋም መለኪያ ጨዋታ በግራ የተከላካይ መስመር ያሰለፉትን የፋሲል ከነማ ክለብ ተጫዋች አምሳሉ ጥላሁንን መቀነሳቸው ታውቋል። በምትኩም የአርባ ምንጭ ከነማው ተካልኝ ደጀኔን  ወደ ቡድኑ መልሰዋል። በቅርቡ ከአርባ ምንጭ ከነማ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተዛዋወረው ታደለ መንገሻ ከቡድኑ ጋር መቀላቀሉም የመሐል ክፍሉን እንደሚያጠናክረው ተገልጿል። ዋሊያዎቹ ጅቡቲን ሱዳን ደግሞ ቡሩንዲን በማሸነፍ ነው የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታቸው ላይ የደረሱት ። የመልስ ጨዋታውንም ከአምስት ቀን በኋላ ወደ ሱዳን  አቅንቶ  የሚገጥም ይሆናል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደርሶ መልስ ጨዋታውን አጠቃላይ ውጤት ማሸነፍ ከቻለ በውድድሩ ተካፋይ ይሆናል። የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና ( ቻን ) የአገር ውስጥ ተጫዋቾች ብቻ የሚካፈሉበት የውድድር መድረክ ነው። ዋሊያዎቹ በሜዳቸው በቀድሞው አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እየተመሩ  ሱዳንን በማሸነፍ ከ 31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለሳቸው ይታወሳል።   ምንጭ

የሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በዝቅተኛ ኑሮ የሚገኙ ሰዎችን ሕይወት እየታደገ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ

Image
ሀዋሳ ነሀሴ 6/2009 የሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በዞኑ በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ሕይወት ለማሻሻል የሚያደርገው ጥረት አበረታች መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱ በሀዋሳ እና በሊቨርፑል ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር የተካሄደ ሲሆን ተቋሙ ያለበትን የመረጃ አያያዝና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጉድለት ፈትሾ ለመፍታት መትጋት እንደሚጠበቅበት ምክረ ሀሳብ ለግሷል፡፡ ጥናቱ በሲዳማ ዞን በሚገኙ ስምንት ወረዳዎች የተካሄደ ሲሆን 397 የማይክሮ ፋይናንስ ተቋሙ ተጠቃሚ አባላትን በመረጃ ሰጭነት አሳትፏል። የሀዋሳ እና በእንግሊዝ የሊቨርፑል ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ቡድን መሪ ዶክተር ከንባታ ባንጋሶ ጥናቱን መሰረት በማድረግ እንደገለጹት ተቋሙ በዞኑ የሚገኙ ድሆችን ሕይወት የማሻሻል ሚናውን በአግባቡ እየተወጣ ነው፡፡ የተቋሙ አብዛኞቹ ተጠቃሚዎች "ተቋሙ ለድሆች የወገነ ውሳኔ እንደሚሰጥና በሚያገኙት የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ዓመታዊ ገቢያቸው ከ20 እስከ 30 ሺህ ብር እንደሚደርስ ምላሽ ሰጥተዋል " ሲሉ መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡ ተጠቃሚቹ በሚወስዱት የገንዘብ ብድር ሰርተው ከመለወጥ ባለፈ በማህበራዊ ኑሮአቸውና በኢኮኖሚ ደረጃቸው መሻሻል በማሳየታቸው በማህበረሰቡ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ከፍ እያለ መምጣቱን ጥናቱ አሳይቷል ። ብድር ከጠየቁ ተጠቃሚዎች ውስጥ 97 ከመቶ የሚሆኑት ብድር ማግኘታቸውንና የመመለስ አቅማቸውም 98 በመቶ መድረሱን ጥናቱ አሳይቷል። በተጨማሪም 84 በመቶ የሚሆኑት የአገልገሎቱ ተጠቃሚዎች ወንዶች መሆናቸው በሴቶች ተሳትፎ ክፍተት ያለበት መሆኑ ጥናቱ መጠቆሙን ገልጸዋል። የሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስ በ1998 ዓ.ም ዳግም የተቋቋመና አንድ ሺህ አባላት እንዳሉት ታውቋል። ምንጭ