የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች ወደ ውጭ በቀጥታ መላክ የሚችሉበትን ስምምነት ፈጸሙ

የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች ወደ ውጭ በቀጥታ መላክ የሚችሉበትን ስምምነት ፈጸሙበአዲሱ የቡና ንግድ አዋጅ መሠረት አቅራቢና ላኪዎች በጋራ እንዲሠሩ ባስቀመጠው ሥርዓት በመጠቀም፣ የደቡብ ቡና አቅራቢዎች ዘርፍ ማኅበር ከመንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በገባው ስምምነት መሠረት ቡናን በቀጥታ መላክ የሚችልበትን ዕድል አስጠብቋል፡፡
ስምምነቱ ማክሰኞ፣ መጋቢት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. በተፈረመበት ወቅት እንደተገለጸው፣ የስምምነቱ ዓላማ ቡና አቅራቢዎች ከላኪዎች ጋር በመሆን ቡናቸውን በቀጥታ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንዲችሉ የሚያበረታታ የአሠራር ሥርዓትን ለማስፈን ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አቅራቢዎች ከአምራቾች ያሰባሰቡትን ቡና በቀጥታ ወደ ውጭ ለመላክ ይቸገሩ እንደነበር የቡና አቅራቢዎቹ አማካሪ አቶ ብሩክ ቢተው ገልጸዋል፡፡ ከቡና አላላክ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ሲታይ የቆየውን የገበያ ችግር አዲሱ አዋጁ በመቅረፉ፣ የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች እንደ አቅራቢ፣ ኮርፖሬሽኑም እንደ ገዥ በመሆን ቀጥተኛ የንግድ ትስስር የፈጠሩበት የመጀመርያው የግብይት ስምምነት ሆኗል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር