የሲዳማ ቡና የህብረት ስራ ኣምራቾች ምን ይላሉ?

በተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ዉጤታማ ሆነናልበሲዳማ ዞን ፌሮና አከባቢ ገበሬዎች ሁሌ-ገብ የህብረት ስራ ማህበር ሊቀመንበር  አቶ ደስታ መኩካ እንዳሉት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከመንግስትና ባለድርሻ አካላት በሚደረግላቸዉ ድጋፍ የማህበራቸው ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል፡፡
ማህበሩ በ1968 የተመሰረተው በ53 አባላትና 43ሺህ ብር ካፒታል እንደነበር አስታውቀው በአሁኑ ወቅትአራት ሺህ 735 አባላት፣ከ28 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ካፒታል ላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡[...]
ማህበሩ ከአባልና ሌሎችም ቡና ተረክቦ በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጥ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን በመጠቆም ባለፈዉ በጀት ዓመት ብቻ ለማዕከላዊ ገበያ ካቀረበዉ ደረቅና የታጠበ ቡና 12 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ  ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡
[...]የሲዳማ ኤልቶ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ዮሀንስ ህብረት ስራ ማህበራት የአባሎቻቸውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚደረግላቸዉ እገዛ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡
ዩኒየኑ በ1996 ዓ.ም በሰባት ማህበራትና 67 ሺህ መነሻ ካፒታል መመሰረቱን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ አባል ማህበራት 89፣ካፒታላቸው ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡
ዩኒየኑ የአከባቢዉን ስነ ምህዳር መሰረት ዘመናዊ የምርት ማሳደጊያ ግብዓት በማቅረብ ምርትና ምርታማነት የመጨመር ስራ ላይ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው የእንስሳት መኖ በማዘጋጀት ለአርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡
የሲዳማ ቡና አብቃይ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ቁጥጥር ኮሚቴ ሀላፊ አቶ ማሞ ለማ ፌሮና አከባቢ ህብረት ስራ ማህበር የአባሎቹንና የአከባቢዉን ህብረተሰብ ችግር ከማስወገድ ባሻገር ለሌሎች ማህበራት የቁሳቁስ፣ የገንዝብ፣ የእዉቀትና የክህሎት ድጋፍ በመስጠት ግንባር ቀደም ማህበር ነዉ ብለዋል፡፡ 
የፌደራል ህብረት ሰራ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡሱማን ሱሩር እንዳሉት የህብረት ስራ ማህበር አባላትን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ግልጽነት በማስፈን ያስመዘገቡት ዉጤት ሌሎች አርአያ ሊሆን የሚችል በመሆኑ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡
በተለይ የፌሮና አከባቢ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ስራ ማህበር በሀገር ደረጃ የተቀመጠዉን የህብረት ስራ መርሆችን በመተግበር ያሳዩት መልካም አፈጻፀም  በሁሉም ክልል ለሚገኙ ህብረት ስራ ማህራት መሰረት የሚጥል ነዉ ብለዋል፡፡
በደርግ ወቅት የተቋቋሙ ህብረት ስራ ማህበራት ፈርሰው የት እንደገቡ እንደማይታወቅ ገልጸው አስቸጋሪው ወቅት አልፎ አሁን የተገኘው ከፍተኛ መሻሻል ሊበረታታ ይገባል ብለዋል፡፡
የጉብኝቱ ዓላማ ማህበሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በክልልና ፌደራል ደረጃ ሞዴል ሆኖ የተመረጠ በመሆኑ የሁሉም ክልል አመራሮች በመጎብኘት ምርጥ ተሞክሮዎቹን እንደአከባቢያቸዉ ተጨባጭ ሁኔታ ቀምረው እንዲያስፋፉ ለማድረግ ነዉ ብለዋል ፡፡
ከጎብኝዎቹ መካከል የኦሮሚያ ክልል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ምክትል ሀላፊ አቶ ሰለሞን ታደለ በህብረት ስራ ማህበር አባላት መካከል ሊኖር የሚገባዉን ትስስር፣ግልጽነት፣ዉጤታማነት፣የገበያ አማራጭ ላይ እዉቀት ማግኘታቸዉን ተናግረዋል፡፡
ሞዴል ማህበራት በየአከባቢዉ ለመፍጠር የፌሮና አከባቢ ህብረት ስራ ማህበራት ተሞክሮን ቀምሮ ማስፋፋት ብቸኛ አማራጭ መሆን አለበት ብለዋል፡፡
የአፋር ክልል ህብረት ስራ ማህበር ማደራጃና ማስፋፊያ  ፅህፈት ቤት የፕላንና ፕሮግራም ክፍል ሀላፊ ወይዘሮ ሀሊማ አሊ የማህበሩ ተሞክሮ እንደ አፋር ላሉ ታዳጊ ክልሎች ያለባቸውን ክፍተት ለማስወገድ በቂ መነሻ ያገኙበት ነዉ ብለዋል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ከ67 ሺህ የሚበልጡ ህብረት ሰራ ማህበራትና ከ360 የሚበልጡ ዩኒየኖች እንዳሉ ከኤጀንሲዉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኤጄንሲዉን ያለፉት አምስት ዓመታት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ የሚመክር የሶስት ቀናት ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል፡፡
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/economy/item/7808-2015-09-17-17-03-02#sthash.2nt83mvb.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር