ሂልተን ሀዋሳ ሪዞርትና ስፓን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ሂልተን ሀዋሳ ሪዞርትና ስፓን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
hawasa_hilton1.jpgስምምነቱን ሂልተን አለም አቀፍ እና ሰንሻይን ቢዝነስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ናቸው ዛሬ የተፈራረሙት።
በሃዋሳ ሀይቅ ዳርጃ በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው ሂልተን ሃዋሳ ሪዞርትና ስፓ፥ ግንባታው በዚህ አመት ነው የሚጀመረው።
ለግንባታውም 42 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት እንደተያዘለት ነው የሂልተን አለም አቀፍ የአውሮፓና የአፍሪካ የልማት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ፓትሪክ ሲትዝዲቦን የተናገሩት።
የሰንሻይን ቢዝነስ ሀላፊነት የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤትና ፕሬዚዳንት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በበኩላቸው፥ መንግስት በክልሉ የሚያካሂዳቸው ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ሰንሻይንን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችን በተለያዩ የገበያ ዘርፎች እንዲሳተፍ ያግዛል ብለዋል።
ሂልተን ሃዋሳ ሪዞርትና ስፓ 169 ክፍሎች እና ቪላዎችን እንዲሁም 6 የስብሰባ አዳራሾችን የሚያካትት ሲሆን፥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 እንግዶች የመቀበል ስራውን ይጀምራል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር