የደቡብ ክልል አዲሱን ምክር ቤት መሠረተ


Source: www.ethiopianreporter.com
tribe south western Ethiopia1
Bodi New Year or Ka'el ceremony Photo @ www.google.de

ባለፈው ግንቦት ወር ከተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ የደቡብ ክልል ለቀጣይ አምስት ዓመት የሚቆየውን የክልሉን መንግሥት የምሥረታ ጉባዔ አካሄደ፡፡ አዲሱ ምክር ቤትም ተመሠረተ፡፡
በግንቦቱ ምርጫ በክልሉ የተካሄደው የክልል ምክር ቤቱንም ሆነ የተወካዮች ምክር ቤትን ምርጫን ደኢሕዴን/ኢሕኢዴግ ሙሉ በመሉ ማሸነፉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መገለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት አምስተኛው ዙር የክልሉ የመጀመርያ ጉባዔ ተካሂዷል፡፡
በምክር ቤቱ መተዳደርያ ደንብ መሠረት ለክልሉ ዋና አፈ ጉባዔነት ወ/ሮ ሕይወት ኃይሉን በድጋሚ መርጧል፡፡
በተያያዘም ምክር ቤቱ በፍትሕ ቢሮ የቀረበለትን የሥነ ምግባር ደንብ ጥሰት በማዳመጥ በቀረበለት ሪፖርት መሠረት ሁለት የሸካ ዞን ከፍተኛ አመራር አባላት ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን ምንጮች ለሪፖርተር ጠቁመዋል፡፡ ነገር ግን ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል የተባሉት የሁለቱን ሹሞች ማንነትና ተገኘባቸው የተባለውን የሥነ ምግባር ጥሰት ምንጮች ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
የክልሉን የሥራ አስፈጻሚዎች በተመለከተ አዲሱ ምክር ቤት በመስከረም ወር  የምርጫ ሥነ ሥርዓት እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ደኢሕዴንን ጨምሮ አራቱም የገዥው ፓርቲ አባላት በመስከረም ወር የራሳቸውን ጠቅላላ ጉባዔ የሚያካሂዱ ሲሆን፣ ፓርቲዎቻቸውን የሚያስተዳድሩ ሥራ አስፈጻሚዎችንና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎቻቸውን እንደሚመርጡም ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም በኢሕአዴግ ምክር ቤት የሚወከሉ 45 ሥራ አስፈጻሚዎችንና ዘጠኝ የማዕከላዊ ኮሚቴ ተወካዮች እንደሚመረጡም ይጠበቃል፡፡ እናት ድርጅቱ ኢሕአዴግ በበኩሉ ከአባል ፓርቲዎች ጉባዔ መጠናቀቅ በኋላ የራሱን ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚያካሂድ ይጠበቃል፡፡

 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር