ዋሊያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ኡጋንዳን ሊገጥሙ ነው

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የኡጋንዳ አቻውን በወዳጅነት ጨዋታ ሊገጥም ነው።
የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን በ2015ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለማለፍ ከጋና ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ እንዲጠቅመው ነው ከዋሊያዎቹ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርገው።
“ዘ ክሬንስ” የፊታችን ጥቅምት 30 በማንዴላ ብሄራዊ ስታዲየም ዋሊያዎቹን ያስተናግዳሉ።
የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን የበላይ ጠባቂ ኢድጋር ዋትሰን እንደተናገሩት፥ የወዳጅነት ግጥሚያው ከሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው የተሰናዳው።
ከጨዋታው ጎን ለጎን ነፃ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ምርመራ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር እንደሚኖር ተነግሯል።
በኢሜኑኤል አዲባየር ሀገር ቶጎ በደርሶ መልስ የተረቱት ኡጋንዳዎች ከምድብ አምስት አራት ነጥብ እና አንድ የግብ እዳ ይዘው በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፤ ምድቡን ጋና በስምንት ነጥብ ስትመራ ቶጎ በስድስት ነጥብ ትከተላለች። 
ጊኒ በአራት ነጥብ እና በሶስት የግብ እዳ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች።
ስለሆነም ኡጋንዳ ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ እድሏን ለማስፋት ከጋና ጋር የምታደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅባታል።
በማሊ በሜዳው 2 ለ 0 ተሸንፎ ባማኮ ላይ 3 ለ 2 ማሸነፍ የቻለውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መግጠም ከጋና ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ አቋማቸውን ለመፈተሽ እጅግ እንደሚጠቅማቸው ነው የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሚሉቲን ሰርዲዮቪች ሚቾ የተናገሩት።
ምንጭ፦www.fanabc.com

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር